Mols.gov.et

ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎቸ የሚመቻቹ የክህሎት ስልጠናዎች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉና የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸው ሊሆኑ ይገባል፤ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

November 20, 2024
ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎቸ የሚመቻቹ የክህሎት ስልጠናዎች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉና የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸው ሊሆኑ ይገባል፤ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ስደተኞችን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎችንና ተቀባይ ማህበረሰብን በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በፕሮጀክቱ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፡፡ አዲስ አበባ አስተዳደርን ጨምሮ ትግራይ፣ሶማሌ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ ስደተኞችን፣የ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችንና ተቀባይ ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርገው ፕሮጀክት (QEP2) በአውሮፓ ህብረት ፋይናንስ አቅራቢነት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና በጀርመን ኢኮኖሚና ልማት ትብብር እየተተገበረ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ስደተኞችና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል ስልጠናን ከማመቻቸት አንፃር በፕሮጀክቱ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ለፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎቸ የሚመቻቹ የክህሎት ስልጠናዎች ፍላጎትን መሰረት ያደረጉና የሥራ ዕድል የሚፈጠርባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ተጠቃሚዎች ወደ ሥራ ገብተው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችሉ የፋይናንስና ሌሎችንም ተጨማሪ ድጋፎችን ከሌሎች አጋር አካላት የማሰባሰብ ሥራ መሰራት እንደሚኖርበትም አሳስበዋል፡፡ የፕሮጀክቱን ውጤታማነት በመከታተልና በመደገፍ ፣ማነቆዎችን በመፍታት እንዲሁም የፖሊሲ አቅጣጫዎች በማስተግበር ረገድ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) እረጋግጠዋል፡፡ በዕለቱ የክህሎት ስልጠና በወሰዱ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የተመረቱ የተለያዩ ምርቶች ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገቡ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
somSOM
Scroll to Top