Mols.gov.et

የተዘጋጁት የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ተቋማቱ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ እንደሆነ ተገለፀ

July 18, 2024
የተዘጋጁት የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ተቋማቱ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያግዝ እንደሆነ ተገለፀ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ለክህሎት ልማት ዘርፉ የተዘጋጁ ረቂቅ የአሰራር መመሪያ እና ደንቦች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተዘጋጁት ረቂቅ የአሰራር መመሪያና ደንቦች ተቋማቱ የሚሰጡትን አገልግሎት በማቀላጠፍ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ያስችላል ብለዋል፡፡ የተዘጋጁት ረቂቅ የአሰራር መመሪያና ደንቦች ዘርፉ ከተሰጠው አዲስ ተልዕኮ እና ሀገራዊ የአሠራር ስርዓቶ ጋር እንዲጣጣም በጥንቃቄ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
somSOM
Scroll to Top