🔊🚨አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት‼️
January 21, 2026
🔊🚨አስቸኳይ የጥንቃቄ መልዕክት‼️
ይህ ከስር የምትመለከቱት ቻናል የሥራና ክህሎት ቴሌግራም ቻናል አይደለም! 👇
🚨 https://t.me/fdre_mols የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አይደለም! 🚨
አሁኑኑ unfollow በማድረግ ራስዎን፣ ቤተሰብዎንና ዜጎችን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!
ትክክለኛው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡-
✅ https://t.me/FDRE_MoLSofficial
⚠️ ጥንቃቄ
በአሁኑ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርን ስምና አርማ (Logo) በመጠቀም፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያወጣቸውን መረጃዎች በማባዛትና በማስመሰል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ሀሰተኛ የቴሌግራም ገጾች እንዳሉ ደርሰንበታል።
እነዚህ አጭበርባሪ አካላት ተገልጋዮችን የሚያታልሉባቸው መንገዶች፦
👉የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ሽፋን በማድረግ በውስጥ መስመር (Inbox) ያነጋግሩዎታል፣
👉ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደተደወለ በማስመሰል ያልተገባ የገንዘብ ክፍያ ይጠይቃሉ፣
👉የተለያዩ የሐሰት ተስፋዎችን በመስጠት ንፁሃን ዜጎችን ለከፍተኛ ምዝበራ እየዳረጉ ይገኛሉ፣
ትክክለኛውን ገጽ እንዴት መለየት ይቻላል?
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይፋዊ ገጽ የሚከተሉት መለያዎች አሉት፦
✅ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት (Verified Badge) ያለው ነው፣
✅ከ 47 ሺህ በላይ ተከታዮች አሉት፣
✅ማንኛውም ይፋዊ መረጃ በድረ-ገጻችንና በሌሎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችን ላይ ከሰፈሩት አድራሻዎች ጋር የተናበበ ነው፣
🛡 ሌሎችንም ይታደጉ
👉መረጃ ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ፣
👉በስህተት ሀሰተኛ ገጾችን እየተከታተላችሁ ያላችሁ ተገልጋዮች፣ በአስቸኳይ ከገጾቹ በመውጣት (Unfollow በማድረግ) ራሳችሁንና ወገኖቻችሁን ከማጭበርበር ይታደጉ፣
👉መሰል አጭበርባሪ ቻናሎች ካጋጠምዎ መረጃውን ያድርሱን!
✅ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ሁልጊዜ ይፋዊ ገጾቻችንን ብቻ ይከታተሉ!
ጥር 12/2018 ዓ.ም፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
🔗 ለወቅታዊ ትኩስ መረጃ
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
