Mols.gov.et

ፕሮግራሙ ዜጎች እጅና አዕምሮአቸው አስተሳስረው ወደ ተሻለ ህይወት የሚሸጋገሩበት መስፈንጠሪያ ነው:: ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

February 18, 2025
ፕሮግራሙ ዜጎች እጅና አዕምሮአቸው አስተሳስረው ወደ ተሻለ ህይወት የሚሸጋገሩበት መስፈንጠሪያ ነው:: ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ የ2ኛው ዙር ማጠቃለያና የሦስተኛ ዙር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ “ብቃት ዛሬን ለነገ” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው መድረክ የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ያጠናቀቁ ከ13 ሺህ በላይ ወጣቶች ተመርቀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፕሮግራሙ የዕለት ጉርስ ከማግኘት በላይ ዜጎች እጅና አዕምሮአቸው አስተሳስረው ወደ ነገ የሚሸጋገሩበት መስፈንጠሪያ ነው ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሀገር የምትገነባው በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ስራ በክህሎት እንዲመራ የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። ወጣቶች በስራ ላይ ልምምድ ያገኙትን ልምድ እያሳደጉ መሄድ ይገባል ያሉት ክብርት ከንቲባዋ ለፕሮግራሙ ስኬት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከዓለም ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ቀርፆ ከ49ሺ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ፕሮግራሙ ወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ስልጠናዎችን አግኝተው ክህሎታቸውን አዳብረው ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ በማድረግ የከተማዋን የሥራ አጥ ዜጎች ቁጥር የመቀነስ ዓላማ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
somSOM
Scroll to Top