Mols.gov.et

‹‹የጥራት ዓመት ››ግብን ለማሳካት በኢኒስቲትዩቱ የተካሄዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች

April 16, 2026
‹‹የጥራት ዓመት ››ግብን ለማሳካት በኢኒስቲትዩቱ የተካሄዱ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጥናት፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ረገድ የያዘውን ‹‹የጥራት ዓመት ››ግብ ለማሳካት በታቀደው መሠረት በርካታ ሥራዎች ማከናወኑ ተገለፀ፡፡ የኢኒስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ሙሉጌታ(ዶ/ር) እንደሚገለጹት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ውስጥ 12 ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮች ተጠናቀው ለተጠቃሚ እንዲበቁ ተደርገዋል። በተጨማሪም ስድስት ጥናቶች በሂደት ላይ እንደሚገኙና ለ24 ተከታታይ ሳምንታት በተካሄደ የምርምር ሴሚናር 61 የጥናት ሥራዎች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ጠቁመዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የባህል ማዕከል ማቋቋሙና በስነ-ጥበብ ሥራዎች የተቋሙን ገጽታ የመገንባት ሥራ ማከናወኑ እንዲሁም የምሩቃንን የቅጥር ሁኔታና የገበያ ፍላጎትን መሰረት ያደረጉ ዘጠኝ የእሴት ሰንሰለት ጥናቶች መጠናቀቃቸውም ተመላክቷል። የማህበረሰብ አገልግሎትን በተመለከተም ኢንስቲትዩቱ የሙያ ብቃቱን ወደ ህብረተሰቡ በማውረድ ረገድ ተጨባጭ ሥራዎችን አከናውኗል። “አንድ ተጨማሪ ክህሎት ለዜጎች” በሚለው መርሃ-ግብር 368 ሰዎች የሰለጠኑ ሲሆን በሌሎች 11 ተቋማት ደግሞ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች የልል ክህሎት ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል። ከዚህም ባሻገር ተንቀሳቃሽ የንግድ ኪዮስኮችን በመሰራት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ፣ ለማዕድ ማጋራት እና ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና አካል ጉዳተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ሀብታሙ ሙሉጌታ(ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡ መረጃው የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ነው፡፡
somSOM
Scroll to Top