Mols.gov.et

የአዲስ አበባ ከተማ የአሠሪና ሠራተኛ ቋሚ አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ምክክር

September 29, 2026
የአዲስ አበባ ከተማ የአሠሪና ሠራተኛ ቋሚ አማካሪ ቦርድ የሦስትዮሽ ምክክር ተካሄደ የቋሚ አማካሪ ቦርዱ መቋቋም በመንግሥት፣ በሠራተኛ ማኅበራትና በአሠሪ ድርጅቶች መካከል ላለፉት በርካታ ጊዜያት ሲደረግ የቆየው ያላሰለሰ ጥረትና የጋራ ትግል አዎንታዊ ፍሬ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። የቦርዱ መቋቋም ዋነኛ ዓላማም በሦስቱ ወገኖች መካከል መደበኛና ተቋማዊ የሆነ የምክክር ባህልን በማሳደግ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ የሥራ ከባቢ (Workplace Environment) መፍጠርና የከተማዋን አጠቃላይ ምርታማነት ማሳደግ ነው። በምክክሩ ወቅት በከተማዋ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አፈጻጸም ሂደት በሚያጋጥሙ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ የሥራ አለመግባባቶችን ከሕግ ክርክር ይልቅ ቀድሞ በመከላከል፣ በውይይትና በጋራ መፍትሔ የመምራት፣ የሥራ ግንኙነትን የመጠበቅና የተቋማዊ ሦስትዮሽ ትብብርን የማጠናከር አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል። የአማካሪ ቦርዱ በዚህ ደረጃ ተደራጅቶ ምክክር እንዲጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ላሳዩት ከፍተኛ የሥራ አመራር ቁርጠኝነት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ይህ የትብብር መድረክ በከተማዋ የሥራ ዓለም ውስጥ የተቀናጀ ምክክርን፣ የጋራ ኃላፊነትን እና ሰላማዊ የሥራ አካባቢን ለመገንባት የሚያስችል አዲስ ምዕራፍ መክፈቱ ተመላክቷል።
somSOM
Scroll to Top