Mols.gov.et

የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት!

December 18, 2024
የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይት ለምርታማነት! የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከክርክር ይልቅ ምክክርን ያስቀደመ የኢንዱስትሪ ባህል ለመገንባት አዳዲስ ሀሳቦችን ቀርጾ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ምክክሩ በኢንዱስትሪ ውስጥ ለሚከሰቱ ግጭቶች እልባት ከመስጠት እንዲሁም የአሠሪና ሠራተኛን ግንኙነት አሻሽሎ ሁለንተናዊ የኢንዱስትሪ ሰላምን ከማምጣትና ምርታማነትን ከማሳደግ የላቀ ግብ ያለው ነው፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገራችን በሥራ ባህል ዙሪያ ያሉ የአመለካከት ማነቆዎችን በመሻገር እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ፀጋዎች አሟጦ መጠቀምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥን ዓላማው ያደረገ የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን ወደ ሥራ አስገብቷል፡፡ በዚህም የምክክር መድረኩን የሚያመቻቹ የአመቻቾች ስልጠና በየክልሉ ተሰጥቷል፡፡ ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ አስተዳደር የአመቻቾች ስልጠና ከወሰዱ በመኋላ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ ተግባራዊ እያደረጉት ይገኛል፡፡ የተጀመረው የማኅበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይቱ በሥራ ባህል ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ በማምጣት በየአካባቢው የሚገኙ መልካም ዕድሎችን ተጠቅሞ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
somSOM
Scroll to Top