በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የልዑካን ቡድን የአርዳይታ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኘ።
በዚህም መደበኛ የትምህርትና ሥልጠና፣ የኢንተርፕራይዝ እንቅስቃሴ እንዲሁም ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
በሥራ ጉብኝቱ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ዋና ዳይሬክተር እና የፌዴራል ግብርና ኮሌጆች የንግድ ሥራ ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ብሩክ ከድርን ጨምሮ የቦርዱ ዓባላት ተገኝተዋል።