Mols.gov.et

እሳቤዎቻችንን ለማጽናት…

June 4, 2024
እሳቤዎቻችንን ለማጽናት… ባለፉት ሁለት ዓመታት ከክህሎት ልማት፣ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከሰላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ እንደ ተቋም የተሰጠንን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት የሄድንበትን ርቀት ባለፉት 5 ቀናት ከዘርፉ አመራሮች ጋር በጋራ ገምግመናል፡፡ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ ከተጠሪ ተቋማት እና ከክልል የዘርፉ አመራሮች ጋር በነበረን በዚህ መድረክ እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከተቋቋምን ጀምሮ የተከናወኑ ሥራዎችን በጥንካሬና በእጥረት ያሉትን ሥራዎች ለይተን የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል፡፡ በዚህም በሦስቱ ዘርፎች ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ አዳዲስ እሳቤዎችና ቅንጅታዊ ሥራዎቻችን ፍሬ ማፍራት መጀመራቸውን እና የተቋም ግንባታ ሥራችንም ውጤታማ እንደነበር አይተናል፡፡ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና እጥረቶችን ለማረም በሚያስችል መልኩ መዘጋጀት እንዳለበት አንስተን ሂደቱም ፈጠራ የታከለበት ልዩ የአመራር ሥርዓትን የሚከተል፣ አስቻይ ሁኔታዎችን የሚፈጥር፣ ማነቆዎችን የሚፈታ እና አቅሞቻችንን ማብዛት ላይ የሚያተኩር መሆን እንደሚገባው ተግባብተናል፡፡ የሀገር ውስጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሙያ ብቃት ምዘናና የአንድ ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን አገልግሎት አሰጣጥ የማዘመን እና ፈጠራ የታከለበትና ከፍተኛ የማደግ አለኝታ ያለቸውን ኢንተርፕራይዞች በልዩ ሁኔታ መደገፍ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎቻችን መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የኢትጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ይዞ የመጣውን ዕድል አሟጦ መጠቀም እና ለሁሉም ሥራዎቻችን ስኬት መሰረት ሊሆን የሚችለውን ማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን በተቀመጠለት ስታንዳርድ መተግበር በየደረጃው የሚገኘው የዘርፉ አመራር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሥራ መሆኑን ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል ለዘርፉ አመራሮች ተናግረዋል ፡፡
somSOM
Scroll to Top