Mols.gov.et

ኢንተርፕረነረሺፕን ተጠቅመን የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ ለኢንተርፕሩነሮች ምቹ የሆነ ሥነ- ምህዳርን መገንባት ቀዳሚ ተግባራችን ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

November 18, 2024
ኢንተርፕረነረሺፕን ተጠቅመን የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ ለኢንተርፕሩነሮች ምቹ የሆነ ሥነ- ምህዳርን መገንባት ቀዳሚ ተግባራችን ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር ‹‹ኢንተርፕረነርሺፕ ለሁሉም›› በሚል መሪ ሃሳብ የሚከበረው ዓለም ዓቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት በይፋ ተጀመሯል፡፡ ሥነ-ሥርዓቱን በይፋ ያስጀመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባስተላለፉት መልዕክት ዓለም ዓቀፉን የኢንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት የኢንትርፕረነርሺፕ ባህልን ለመገንባትና አስተሳሰቡ ስር እንዲሰድ የሚያስችል እና ከዓለም ጋር መተሳሰሪያ ገመድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ከህዳር እስከ ህዳር በሚል ስያሜ በርካታ ኢንተርፕርነሮችን ለማፍራት የሚያስችል ተግባር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሲከናወን ቆይቷል። በዚህም ከወረዳ ጀምሮ በተካሄዱ የፈጠራ ሃሳብ ውድድሮች 3ሺ ሥራ ፈጣረዎች ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ የሚችሉበት ዕድል መፈጠሩን አስረድታዋል፡፡ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የ‹‹ሠመር ካምፕ ›› ፕሮግራም በፈጠራ ባለቤቶች የተሰሩ የተለያዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማዳበር ለገበያ የማብቃት ሥራ መሰራቱንም ገልፀዋል፡፡ እንደ ሀገር ፈጠራ መር የሆነ የኢኮኖሚ ሥርዓትን ዕውን ለማድረግ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በዘርፉ ልማት ተደራሽ ያልሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎች ለመድረስ የሚያስችሉ ሥራዎች በሚኒስትር መ/ቤቱ እንደሚሰሩም ክብርት ሚኒስትር ጠቁመዋል፡፡ ኢንተርፕረነረሺፕን ተጠቅመን የሀገራችንን ብልፅግና እውን ለማድረግ ለኢንተርፕሩነሮች ምቹ የሆነ ሥነ- ምህዳርን መገንባት ቀዳሚ እንደመሆኑ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር ዘርፉን እንደማህበረሰብ የማሰቢያ መንገድ እንዲሆን በሚያስችል መልኩ ሥነ ምህዳሩን የማመቻቸት ሥራ እንደሚሰራም ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አስረድተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ለኢንተርፕሪነርሺፕ የተሻለ ትኩረት የሰጡ አገራት የተሻለ ኢኮኖሚ ማስመዝገብ መቻላቸውን ዓለም አቀፍ ዕውነት መሆኑን በመጠቆም በሀገራችንም የዘርፉን ልማት በመጠቀም የሚጠበቀውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ምቹ የሆነ የፖሊሲ ስነ-ምህዳር መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ዓለም ዓቀፍ የኢንተርፕረነርሺፕ ሳምንት ከህዳር 9 እስከ 17/2017 ዓ.ም በኤግዚቢሽኖች፣ በፓናል ውይይቶችና በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
somSOM
Scroll to Top