ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት እየተከናወነ የሚገኝ ፋና ወጊ ሥራ
September 19, 2025

ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት እየተከናወነ የሚገኝ ፋና ወጊ ሥራ
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሀገራዊ የክህሎት ልማት ሥራን ማሳለጥ የሚያስችሉ ሰፋፊ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ተቋሙ የሀገሪቱ የክህሎት ልማት የሚያጎለብቱ ብቃት ያላቸው አሰልጣኞች ለማፍራት ጥራት ያለው ስልጠና መስጠት የሚስችለውን የሰልጣኝ-አሰልጣኝ ጥምርታ አንድ ለ20 ሰልጣኝ እና የተማሪ የስልጠና ወርክሾፕ ጥምርታ አንድ ለ15 ሰልጣኝ ማድረስ ችሏል፡፡
የአሰልጣኝ መምህራን ምጣኔ ደግሞ 71 በመቶ ሁለተኛ ዲግሪና 29 በመቶ ሶስተኛ ዲግሪ አድርሷል፡፡
ይህም ሀገራችን የምትፈልገው ብቁ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ምቹ መደላድል የሚፈጥር ነው፡፡
ከዚህም ባሻገር ኢንስቲትዩቱ ከሚሰጠው ተግባራዊ ስልጠና ጎን ለጎን አስተማሪ የሆኑ የልማት ስራዎች በቅጥር ግቢው እያከናወነ ይገኛል፡፡
በተለይ ተቋሙ የጀመረው የተቀናጀ ግብርና (integrated farm) ፕሮጀክት ሥራ በቬርቲካል ፋርሚንግ፤ በጓሮ አትክልት፤ ግሪን ሃዉስ፤ በወተት ከብት ዕርባታ፤ በዓሳ እና የዶሮ ዕርባታ ኤስ ኤን ቪ ከተባለ ድርጅት ጋር በትብብር እጅግ አበረታች ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህም ባሻገር ተቋሙ የአጋር አካላትና ተቋማት ትሥሥር ከማጠናከርና ውጤታማነትን ከመጨመር አኳያ በቻይና ሃገር ከሚገኘዉ ጂያንግሱ የግብርናና ደን ቴክኒክል ኮሌጅ ጋር በመተባበር በወተት ማቀነባበር ቴክኖሎጂ (Dairy processing technology) የጥምር ዲግሪ ፕሮግራም እየሰጠ ይገኛል፡፡
በተቋሙ ስማርት የማኑፋክቸሪንግ ፓይለት ማሳያ ፕሮጀክት አማካይነት ዘመኑን የዋጁ 3D printer machine, welding simulation machine, CNC Simulation Machine, PCB Machine እና Axis CNC Machine በመጠቀም የስማርት ማኑፈክቸሪንግ ሥራ ሂደት እየተሳለጠ ይገኛል፡፡
ተቋሙ በትኩረት እየሰራው ከሚገኙት ስራዎች መካከል ተጠቃሽ የሆነው ፋብርኬሽን ኢንጅነሪንግ ውስጥ ለወርቅ ማዕድን ማውጫ የሚያግዙ ማሽኖች መካከል Milling Machine ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለብዝሃ ምርት (Mass production) ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ተልኳል፡፡
በተቋሙ ቴክኖቢዚያ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተዋቅሮ በአራት ዋና ዋና ዘርፎች ማለትም በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በቢዝነስ ልማትና ኮሜርሻላይዜሽን እንዲሁም በሃብት አስተዳዳር በልማት ድርጅት ተመዝግቦና ህጋዊ ፈቃድ ወስዶ ተቋሙ የሚሰጣቸውን ስልጠኛዎችን የሚደግፍ በቦርድ የሚመራ ኢንተርፕራይዝ ወደ ስራም ገብቷል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የስልጠና ጥራት ለማረጋገጥ በሰራው ውጤታማ ስራ የአይሶ 9001፡2015 ሰርተፍኬት ባለቤትም ሆኗል፡፡






