Mols.gov.et

በ47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር ተሳትፎ ላደረገው የልዑካን ቡድን እውቅና ተሰጠ

October 3, 2024
በ47ኛው የዓለም የክህሎት ውድድር ተሳትፎ ላደረገው የልዑካን ቡድን እውቅና ተሰጠ በአዲሱ ዓመት መባቻ ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው ዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር ተሳትፋለች፡፡ በመድረኩ ኢትዮጵያ በሦስት የሙያ መስኮች ተወዳዳሪዎችን አሳትፋለች፡፡ በዚህም በICT and Networking ጽዮን አዳነ፣ በCNC Machine የሮም ነሽ አዋሬ እና በFurniture Making ብሩክ ፀጋዬ ሀገራችንን ወክለው ተሳትፎ አድርገዋል፡፡ በICT and Networking ተወዳዳሪ የነበረችው ፅዮን አዳነ በመድረኩ “Best of Nation recognition” ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች፡፡ ከመድረኩ ተሳትፎ በርካታ ልምዶችን ማግኘት እንደተቻለ የተጠቆመ ሲሆን ለተሳታፊዎች፣ የልዑኩ ቡድን አስተባባሪዎች እና ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ክህሎት ማህበረሰብ አባል ሀገር እንድትሆን ጥረት ላደረጉ አመራሮች ከክብርት ሚኒስቴር የምስጋና እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
somSOM
Scroll to Top