Mols.gov.et

በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል ውይይት በኳታር ዶሃ ተካሄደ

May 27, 2024
በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል ውይይት በኳታር ዶሃ ተካሄደ፡፡ ውይይቱ በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴን እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤ ተሬሳ የተመራ ልዑካን ቡድን በ‹‹ዶሃ ውይይት›› ያደረገውን ተሳተፎ አጠናቆ ተመልሷል፡፡ በመድረኩ የሠራተኞች እንቅስቃሴን ደህንነቱ የተጠበቀና ቀልጣፋ ከማድረግ ባለፈ በላኪና ተቀባይ ሀገራት መካከል ፍትሃዊ የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አስተዳደር አስፈላጊነት ላይ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ የልዑካን ቡድኑ አመላክተዋል፡፡ በኳታር ዶሃ የተካሄደው ይህ ውይይት በአፍሪካና በባህረ ሰላጤው ሀገራት መካከል ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ የሠራተኞች እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነም ነው የልዑካን ቡድኑ ያመላከቱት፡፡ በመድረኩ ዮርዳኖስ፣ ሊባኖስ፣ እና የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት አባል ሀገራት እና የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ የ33 ሀገራት ተወካዮች እና ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡
somSOM
Scroll to Top