Mols.gov.et

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

July 16, 2025
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በራስ ፀጋ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ገለጹ። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በመንግስት እና በፓርቲ ትብብር የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚገመግም መድረክ በድሬደዋ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት እና የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራሮች፣ ሚኒስትሮች እና የየክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። ከተረጅነት የመውጣት ጥረት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የገበያ ማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን በመቀነስ ረገድና ሌሎች ጉዳዮችን በመዳሰስ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተመዘገቡ ውጤቶችን በተመለከተ በስፋት ውይይት ተደርጓል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤ ለዜጎች በውጭና ሀገር ውስጥ የስራ እድል በማመቻቸትና በመፍጠር ረገድ የተሳካ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል። በኢትዮጵያ ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲኖር በማድረግ ዜጎች በቀሰሙት ዕውቀትና ክህሎት ለሀገር ከፍታና ብልፅግና መረጋገጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ከሥራ ዕድል ፈጠራም ባለፈ በሌሎች ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፥ በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)፥ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በፓርቲና በመንግስት ትብብር የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አንስተዋል። በመሆኑም የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል በተያዘው በጀት ዓመትም የላቀ አፈፃፀም እንዲኖር የተቀናጀ ጥረት ይደረጋል ብለዋል። የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ(ዶ/ር) በበኩላቸው፥በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የሀገሪቷን ዘርፈ ብዙ ልማትና እድገት ማሳለጥ መቻሉን አንስተዋል። የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ረገድ በስፋት ጥረት መደረጉንም ጠቅሶ የዘገበው ኢዜአ ነው። ሀምሌ 9/2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
somSOM
Scroll to Top