Mols.gov.et

ኢንተርፕራይዞች …

April 29, 2026
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የክልሉን ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ከፈቱ። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ ለሚቀጥሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆየውን የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር ከፍተዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ በአዲስ መልክ ለሁለተኛ ጊዜ በሚያካሄደው ኢግዚቢሽንና ባዛር የሞዴል ኢንተርፕራይዞች የደረጃ ሽግግርና ዕውቅና ፕሮግራም እንደሚኖር ቢሮው አስታውቋል ። በባዛሩ በኢንዱስትሪና በግብርና የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን አጋጣሚው አምራቾችና ሸማቾች በቀጥታ የሚገናኙበት ሰፊ የገበያ ትስስር የሚፈጥር እንደሚሆንም የቢሮው ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ አስታውቀዋል፡፡ በዝግጅቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
somSOM
Scroll to Top