Mols.gov.et

በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ

December 5, 2024
በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ ተጠቆመ በህዳር ወር የሚከበሩት የሴቶችና የህጻናት፣ የአረጋውያን እና የኤች አይቪ ኤድስ ቀን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተከብሯል፡፡ በመድረኩ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሐንስ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶችና ህጻናት ከሃገሪቱ ህዝብ ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ገልጸው በእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ከግለሰብ ጀምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በየደረጃው በጋራ መቆም ይገባል፡፡ አካል ጉዳተኞች ያላቸውን እምቅ አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ ማገዝ፣ የክህሎት ባለቤት እንዲሆኑ ስልጠና እንዲያገኙ ማስቻል እና የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መስራት ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ኤች አይቪ ኤድስ አምራች ዜጎችን እየቀጠፈ የሚገኝ በመሆኑ ከመዘናጋት መውጣት እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
somSOM
Scroll to Top