Mols.gov.et

መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠው ትኩረት የኢትዮጵያን እውነት በመግለጥ ኢንዱስትሪውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚንስትር

July 10, 2025
መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠው ትኩረት የኢትዮጵያን እውነት በመግለጥ ኢንዱስትሪውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚንስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የካበተ ልምድ ካለው ቦስተን ፓርትነርስ (ኩሪፍቱ ሪዞርት) ጋር በዘርፉ በትብብር መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት መንግስት ለቱሪዝም ዘርፍ የሰጠው ትኩረት የኢትዮጵያን እውነት በመግለጥ ኢንዱስትሪውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችል ነው፡፡ ስምምነቱ ዘርፍ አሁን የደረሰበትን ደረጃ በሚመጥን መልኩ የሰው ሀይል ለማዘጋጀት፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ለዓለም ለመግለጥ እና በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ትልቅ ፋይዳ ይረዋል፡፡ በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት በኩል በዘርፉ የሚሰማሩ በርካታ የሰው ሃይል የማሰልጠን ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የጠቆሙት ክብርት ሚንስትር ሰልጣኞች በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ሥራ ሲሰማሩ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ታሳቢ ባደረገ መልኩ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል፡፡ የቦስተን ፓርትነር ግሩፕ (ኩሪፍቱ ሪዞርት) መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ታዲዮስ ጌታቸው በበከላቸው ስምምነቱ በዘርፋ ምንም ልምድ የሌላቸውን ሰልጣኞች በቂ ክህሎት ታጥቀው እንዲወጡ ከማዘጋጀት ጀምሮ በዘርፉ የተሰማሩ ዜጎችን ለማብቃት ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ሀምሌ 3/2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
somSOM
Scroll to Top