Mols.gov.et

ለጥንቃቄ!

November 25, 2024
ለጥንቃቄ! ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፡፡ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጫት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን እየገለጽን ዜጎቻችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት ከፈለጉ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
somSOM
Scroll to Top