Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞችንና…

October 16, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶች፣ የወጣቶች፣ የአካል ጉዳተኞችንና የሌሎችም የጋላጭ ህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተያዙ ዕቅዶችን ለማናበብ የሚያስችል የውይይት መድረክ ከተጠሪና ከክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት ጋር ተካሂዷል፡፡ በመድረኩ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሪት መነን መለሰ ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በክህሎት ልማትና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፎች የሚስፈፅማቸው ተልዕኮዎች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የሚመለከቱ እንደመሆናቸው በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚታቀዱ ዕቅዶች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ማካተታቸውን የማረጋገጥ ሥራ በቋሚነት እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመደበኛ ዕቅዶቹ ከሚያስፈፅማቸው ተልዕኮዎቹ ጎን ለጎን በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎቹ በሶማሌ ክልል የመማሪያ ክፍሎችንና ግንባታና የአቅመ ደካማ ነዋሪዎችን ቤት የማደስ ሥራ ማከናወኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ በአዲስ አበባ ከተማ 54 አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ባለ አራት ወለል ህንፃ የመኖሪያ ቤት አስገንብቶ ለከተማ አስተዳደሩ ማስረከቡንም ገልፀዋል፡፡ በየደረጃው የሚገኙ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪና የክልል የዘርፉ አስፈፃሚ ተቋማት ከህብረተሰቡ ጋር በቀጥታ የሚገናኙ መሆናቸውን መነሻ በማድረግ የዘርፉን አካታችነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ጉዳዮችን በጥናት ከመለየት፣ በዕቅድ ከማካተትና ከማስተግበር አንፃር ያሉበትን ደረጃ ለመፈተሸና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ወ/ሮ እርቅነሽ ዮሃንስ በበኩላቸው ከጠቅላላው የሀገራችን የህዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ ድርሻ ያላቸውን ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን ያላካተተ ማንኛውም ሀገራዊ ዕቅድ የዜጎችን ሙሉ ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ስለማይጠበቅ በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት ዕቅዳቸውንና አፈፃፀማቸውን በየጊዜው መፈተሽና የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የላቀ ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top