Mols.gov.et

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።

May 27, 2023
ክህሎት ለተወዳዳሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል። ውድድሩ ፍፃሜውን ሲያገኝ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ከአንድ መቶ ሺህ እስከ 60 ሺህ ብር ድረስ የማበረታቻ ሽልማት፣ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስራ ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት አንደኛ በመውጣት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል። የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዘጠኝ ወርቅ፣ አስር ብር እና ሰባት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ሰባት ወርቅ፣ ስምንት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል።
oroORO
Scroll to Top