የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለሚኒስቴር መ/ቤቱና በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ለሚደረግላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ስጦታ አበረከቱ፡፡
September 9, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ለሚኒስቴር መ/ቤቱና በሚኒስቴር መ/ቤቱ ድጋፍ ለሚደረግላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች የበዓል ስጦታ አበረከቱ፡፡
ክብርት ሚኒስትር የበዓል ስጦታውን ያበረከቱት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየካ አካባቢ በቋሚነት ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ህፃናትና ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሰራተኞች ነው፡፡
ጤፍ፣ ዶሮ፣ እንቁላልና ዘይትን ባካተተው የባእል ስጦታ ከ630 ሰላሳ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎች ማዕድ ተጋርተዋል።
በስነሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በ2016 በጀት ዓመት የሚኒስቴር መ/ቤቱን ተልዕኮ ከማሳካት አንፃር ታላላቅ ስኬቶች የተገኙበት ዓመት እንደነበረ ገልፀዋል፡፡
‹‹ዓመተ ምርታማነት ›› ተብሎ በተሰየመው የ2016 በጀት ዓመት በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነት ረገድ ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
‹‹ዘመነ ማፅናት›› የሚል ስያሜ በተሰጠው የ2017 በጀት ዓመት የተገኙ ውጤቶችን በማፅናት ለዜጎቿ ምቹ የሆነችና ኢኮኖሚያዊ ሉአላዊነቷን ያረጋገጠች ሀገር ዕውን ለማድረግ በህብረት፣ በጋራና በአንድነት እንቁም የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡