Mols.gov.et

ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር…

March 17, 2025
ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር… ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ ጋር በትብብር መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይታችን በሰው ሃይልና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም ሥራ ዕድል ፈጠራና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ከመፍጠር አኳያ በቅንጅት ልንሰራቸው የሚችሉ በርካታ ሥራዎች እንዳሉ ተመልክተናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ጨምሮ በቀጣይ በጋራ በሚለዩ የትብብር መስኮች ላይ በቅንጅት ለመስራትም ተግባብተናል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ በቅንጅት በመሥራት የተቀመጡ ሀገራዊ ግቦችን በማሳካት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማላቅ ላሳዩን የላቀ ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
oroORO
Scroll to Top