Mols.gov.et

”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

February 2, 2023
”በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በዘርፉ ተወጥነዉ እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ እሳቤዎች ላይ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሠው ሃብት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዓለም አቀፍ፣ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ዕድሎችና ፈተኛዎችን በመለየት ፈተናዎቹ ወደ ዕድል፤ ዕድሎችን ደግሞ ለመጠቀምና ወደ ዉጤት ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ በዚህም በዘርፉ ዘላቂ ለዉጥ ለማምጣት ዛሬና ነገን ያማከሉ ሥራዎች በማስተሳሰር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የዘርፉን ስራዎች ግብ እንዲመቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ያላቸዉ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top