Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አገልግሎትን ለማሻሻል …

November 4, 2026
የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ለማሻሻልና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ ክቡር አቶ አወሉ አብዲ – የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ላይ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታትና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር አቶ አወሉ አብዲ ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህን የገለጹት ከሚኒስቴሩ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ላይ በተስተዋሉ ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ በተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ነው። በውይይቱ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱን ችግሮች፣ መንስኤዎቻቸውንና የመፍትሔ አማራጮችን የሚያብራራ ሰነድ ቀርቦ ዝርዝር ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ለሀገር ትልቅ ሀብት መሆኑን ጠቁመው ሥርዓቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካትም ትልቅ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል። በሥራ ገበያ መረጃ ስርዓቱ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በጥልቀት መለየትና በቅድሚያ መፍትሔ የሚያስፈልጋቸውን ችግሮች መለየት እንደሚገባም ገልጸዋል። ችግሮቹ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በተዘጋጀ አቅጣጫ መፍትሔ እንዲያገኙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል። ከቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር፣ ከሰው ኃይልና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ከሕግና አሠራር ጋር የተያያዙ ችግሮች በአስቸኳይ ተለይተው እንዲቀርቡም አሳስበዋል። እነዚህን ችግሮች በየደረጃው በመፍታት ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት በትኩረት መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ችግሮቹ እስኪፈቱ ድረስ አገልግሎቶች መቋረጥ የለበትም ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ክፍተቶቹን እየፈቱ አገልግሎቶች እንደሚሰጡ አብራርተዋል። በውይይቱ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላትና የዘርፉ መካከለኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
oroORO
Scroll to Top