Mols.gov.et

ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተባለ፡፡

October 23, 2024
ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ተባለ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እያካሄደ የሚገኘው የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የክልሎች አፈፃፀም ግምገማን ቀጥሎ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የሱማሌ ክልል አፈፃፀምን ተመልከቷል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኮቹ ላይ ባስተላለፉት መልዕት፣ እንደ ዘርፍ በጀት ዓመቱ በስፋትም ሆነ በይዘቱ የተለየ ሥራ የምንሰራበት እንደሆነ ተግባብተን ወደ ተግባር ገብተናል፡፡ በዚህ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከተለመደው አሰራር የተላቀቀ አካሄድ እንዲሁም የተለየ የድጋፍና የክትትል ሥራ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡ በሦስቱም ዘርፎች የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የተጀመሩ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚገባ ያመላከቱት ክብርት ሚኒስትር ዜጎች በአምስት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉና የርቀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top