Mols.gov.et

የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫው የማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንዲሰጡ እየተደረገ ያለውን ጥረት ማሳያ መሆኑ ተገለፀ

November 14, 2024
የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫው የማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንዲሰጡ እየተደረገ ያለውን ጥረት ማሳያ መሆኑ ተገለፀ የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ‹‹ ISO 9001:2015 ›› የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬት አገኘ፡፡ የጥራት ሥራ አመራር ማረጋገጫ ሰርተፊኬቱን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ለኮሌጁ አስረክበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ነቢሃ ሙሃመድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በየደረጃው ያሉ ተቋሞቻችን ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም ሚኒስቴሩ 20 ተቋማትን ዓለም አቀፍ መመዘኛዎችን እንዲያሟሉ በእቅድ ይዞ ሲሲራ የቆየ ሲሆን እስካሁን የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ 5ቱ የISO 9001:2015 የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህም እንደ ዘርፍ የማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና እንዲሰጡ እየተደረገ ያለውን ጥረት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው፤ ድሬዳዋ የኢንደስትሪ ኮሪደር እንደመሆኗ ኮሌጁ ብቁና ተወዳዳሩ ባለሙያዎችን ማፍራት እንደሚጠበቅበት ጠቁመዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጥራት ያለው የሰው ሃይል ለማፍራት፤ ጥራት ባለው የትምህርት ስርዓት እና ምዘና ማለፍ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top