Mols.gov.et

የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል ገለፁ።

November 22, 2022
የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጪ የሆነ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርህያት ካሚል ገለፁ። ሚኒስትሯ ይህን የገለፁት በደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘውን የካርቪኮ ጨርቃጨርቅ ማምረቻ ፋብረካን በጎበኙበት ወቅት ነው። በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው የካርቪኮ ጨርቃጨርቅ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ዘመናዊ ማሽኖችን ከመትከል ባሻገር ሰራተኞቹን በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ስልጠናዎች እንዲበቁ አድርጓል፡፡ የስራ ላይ ደህንነትና ጤንነትን እንዲሁም የአካባቢ ደህንነትን ለመጠበቅ ድርጅቱ እያደረገ ያለው ጥረት በተሞክሮነት የሚነሳ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ሙፈርህያት ይህ ጥረት ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆንና የግሉ ዘርፍ ተስፋ ሰጭ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን የሚያመላከት ነው ብለዋል፡፡ በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አጉስቲኖ ፓሌሲ ተገኝተዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top