Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀማችንን ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት ገምግመናል

April 23, 2025
የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዕቅድ አፈፃፀማችንን ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት ገምግመናል፡፡ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተካሄደው በዚህ መድረክ ከሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦት፣ ከሥራ ገበያው ፍላጎት እና ከአገልግሎት አሰጣጥ አኳያ የተከናውኑ ሥራዎች ላይ በዝርዝር ተወያይተናል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ ከእስከ መጋቢት 30 ድረስ 359 ሺህ 291 ዜጎችን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ካለው የሥራ ገያ ፍላጎት አኳያ አቅርቦት እና ጥራት ላይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት ውጤቱን ለማላቅ እና የዜጎችን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም ተግባብተናል፡፡ በዘርፉ በመንግስትና በግል ተቋማት የሚሰጠው ሥልጠና የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልስ እና ፍላጎትና አቅርቦቱን ማጣጣም የሚያስችል መሆኑን የማረጋገጥ እንዲሁም ማነቆዎችን መፍታትና ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችን ዋነኛ ማጠንጠኛ ሆኖ ተለይቷል፡፡ በዘርፉ የተጀመረው የዜጎችን መብት ደህንነትና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ህገ-ወጥነትን መከላከልና ህግና ስርዓትን ማስከበርም በልዩ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ ለዚህም በየደረጃው የሚመለከታቸው ባለደርሻና አስፈፃሚ አካላት ሁሉን አቀፍ ርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እየሰጡ ላለው ውጤታማና ጠንካራ አመራር እንዲሁም ሚናችሁን እየተወጣችሁ ላላችሁ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ! የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
oroORO
Scroll to Top