Mols.gov.et

የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

July 23, 2024
የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ግብ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው። ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 እና 123/13 ለማሻሻል የሚያስችል የግብዓት ማሰባሰቢያ የውይይት መድረክ ከውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ኤጀንሲ ማህበራት ተወካዮች ጋር በሚኒስቴሩ አዳራሽ አካሄዷል፡፡ በግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዳንኤል ተሬሳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ የውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት ዜጎች መብታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ አገር እንዲሰማሩ በማደረግ ዜጎችና እና ሀገራችን ከውጭ አገር ሥራ ሥምሪት የሚገባውን ጥቅም እንዲገኝ መሆኑን ገልጸው አሁን ሥራ ላይ ያለውን የዘርፉ አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ምክንያት አሁን ካለንበት ጊዜ ጋር ሊያሰራ የሚችል ዘመናዊ ቀልጣፋ አሰራር ለመዘርጋት ያለመ ነው፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት እንዲታገዝ በማድረግ እጅግ ውጤታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የሚሻሻለው አዋጅ ህጋዊ የስራ ስምሪቱን በማጠናከር የህገወጥ ሰዎች ዝውውርን በመግታት በኩልም ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ አዋጁ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግና አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ሁሉ በውስጡ ያካተተ እንዲሆን ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉበት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top