Mols.gov.et

የክህሎት ስልጠና ለወሰዱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር …

September 23, 2024
የክህሎት ስልጠና ለወሰዱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ገለፀ፡፡ በቢሮው የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ም/ል ኃላፊ አቶ ካንቹላ ካንቤ እንደገለፁት ሥራ ፈላጊዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ከሚገኘው SHINTS ETP GARMENT PLC Ethiopia የተሰኘው ካምፓኒ ጋር በማስተሳሰር የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው ይገኛል፡፡ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክና በሌሎችም አካባቢዎች የሥራ ልምድ ያላቸውን ብቁ ባለሙያዎች የመመዝገብና ከሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር ብቃታቸውን የማስመዘን ሥራ በቢሮው እየተከናወነ እንደሚገኝም አቶ ካንቹላ ገልፀዋል፡፡ ቢሮው ከጋርመንት ፋብሪካው ጋር ከባለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ ሲሠራ የቆየ ሲሆን በጋርመንት ዘርፍ ለሰለጠኑና ብቃታቸው በምዘና ለተረጋገጠ 1,217 ለሚሆኑ ባለሙያዎች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ከቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡፡፡
oroORO
Scroll to Top