Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር …

March 5, 2026
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጋር የአቪዬሽን ባለሙያዎችን ማብቃትና ማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአቪዬሽን ዘርፍ የሰው ኃይል አቅርቦት፣ ስልጠና እና ስምሪት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ ስምምነቱ የኢትዮጵያ ወጣቶች በዘርፉ አሰልጥኖ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ብቁ አድርጎ ማቅረብ የሚያስችል ነው። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ የከባተ ልምድ ያለውን የኢትዮጵያ የአየር መንገድ ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በሌሎችም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለአቬሽን ዘርፉ ብቁ ወጣቶችን አሰልጥኖ ለሀገር ውስጥና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ባይ በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ በዓመት ከ3 ሺህ እስከ 4 ሺህ የሚደርስ አዲስ ሠራተኛ እንደሚቀጥር ጠቁመዋል። ሰራተኞችን የመመልመል እና የማሰልጠን ሂደት አድካሚና ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር መሥራት የሥራ ድግግሞሽን ከማስቀረቱም በላይ የሀገሪቱን ወጣቶች በአግባቡ በማብቃት ተወዳዳሪ ዜጎችን መፍጠር ያስችላል ብለዋል። ከኮቪድ-19 በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአቪዬሽን ባለሙያዎች እጥረት እንዳለ የገለጹት ኃላፊው ይህንን ክፍተት ለመሙላት በቂ እና ብቁ ወጣቶችን ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እና በቅንጅት ማሰልጥን ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በዚህ ስልጠና የሚያልፉ ወጣቶች በዋናነት ለኢትያጵያ አየር መንገድና ለሌሎችም ሀገራት አቬየሽን የማቅረብ ሥራ በስፋት እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡ ይህ ስምምነት የዜጎችን ሙያዊ ብቃት በማጎልበት በማሳደግ፣ በየትኛውም የዓለም ብቁ ተወዳዳሪ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል፡፡ በቀጣይም የመግባቢያ ስምምነቱ ወደ ዝርዝር ዕቅድ ተቀይሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።
oroORO
Scroll to Top