Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ከቤተሰብ አባላቶቻቸው ጋር በጋራ ሆነው ተቋማዊ የቤተሰብ ቀንን አከበሩ።

October 3, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች ከቤተሰብ አባላቶቻቸው ጋር በጋራ ሆነው ተቋማዊ የቤተሰብ ቀንን አከበሩ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ፕሮግራሙን በይፋ ሲከፍቱ ባስተላለፉት መልዕክት የሚኒስቴር መ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልዕኮ ለመወጣት ለሚያደርጉት ጥረት ስኬታማነት የቤተሰብ አባላት ድጋፍ ወሳኝ ነው። በመሆኑም አንድ ተቋም ውስጥ የሚሠሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት እንደመሆናቸው የተቋሙ ሠራተኞች ብቻ ሳይሆን ቤተሠብቻቸውም ጭምር ተገናኝተው የጋራ ጊዜ የሚያሳልፉበት ጊዜ ስለሚያስፈልግ መድረኩ ተዘጋጅቷል ብለዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎች የተሻለ ህይወት ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ የሚተጋ ተቋም መሆኑን የጠቀሱት ክብርት ሚኒስትር ተቋሙ ለሚጠብቀው ረጅም ጉዞ ስኬታማነት የቤተሰብ አባላት የሚያደርጉት ድጋፍ ተጠናከሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። በሚኒስትር መ/ቤቱ የሚካሄደው የቤተሰብ ቀን ተቋማዊ ባህል ሆኖ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
oroORO
Scroll to Top