Mols.gov.et

የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ለቴክኒክና ሙያ ድጅታላይዜሽን

May 10, 2025
የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ለቴክኒክና ሙያ ድጅታላይዜሽን ኢትዮ ክህሎት 2017 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲካሄድ ቆይቶ ነገ መቋጫውን ያገኛል። አምስተኛ ቀኑን የያዘው ይህ የክህሎት ውድድር በዛሬው ውሎው ዘርፉ ላይ ያተኮሩ ሁለት የፓናል ውይይቶች ተካሂደዋል። ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተካሄደው የፓናል ውይይት የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠ ድጅታላይዜሽን(public private partnership for TVET Digitalization) የሚል ርዕስ የተሰጠው ነበር። የሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መርሃ ግብር አካል የሆነው ይህ ፓናል ውይይት በዘርፍ ላቅ ያለ ልምድ ያላቸው ፓናሊስቶች የተሳተፉበት ሲሆን የዘርፉ አመራሮች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት ታድመውበታል። በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሥልጠና ስርዓት በድጅታል ቴክኖሎጂ ለማገዝ መንግስትና የግሉ ዘርፍ ተባብረው የሚሰሩባቸው ሁኔታዎች ተመላክተዋል። የዘርፉ የሥልጠና ስርዓት ለማዘነንም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተጠቁሟል። በጠዋቱ መርሃ ግብር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀመረው በልምድ የተገኘ ክህሎት ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።
oroORO
Scroll to Top