Mols.gov.et

ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ ተግባር ተኮር የሙያ ዘርፎች

August 13, 2026
ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ ተግባር ተኮር የሙያ ዘርፎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተሻሻለው የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ከተቀመጡ ቁልፍ ስትራቴጂዎች መካከል ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ዜጎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን እንዲያገኙ ማስቻል(vocationalization አንዱ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ፣ በመደበኛ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረጉት 11 የሙያ ዘርፎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፣ የሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት ተካሂዷል፤ በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ መስተዳድር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ አዲሱ አሰራር ተማሪዎችን በክህሎት በመቅረጽ አምራች ዜጋ ለማፍራት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ የዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ በበኩላቸው ገበያው የሚፈልገው በክህሎት የበቃ የሰው ኃይል ለማቅረብ የተቀናጀ ሥራ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። ለሙያ ዘርፎቹን ለመተግበር የሚያስችል የመርሃ ትምህርት፣ የተማሪ ሞጁል እና የመምህር መመሪያ ዝግጅት በትምህርት ሚኒስቴር ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡ በዚሁ መሠረት ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ብረታ ብረት ፣ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አልባሳት ቴክኖሎጂ፣ ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፣ ቧንቧ ሥራ፣ ሶፍትዌር ማበልጸግ፣ ሰብል አመራረት፣ ጤና ክብካቤ አገልግሎት፣ ሆቴል አገልግሎት፣ ፀጉር ሥራና ውበት አገልግሎት እና ምግብ ዝግጅት የመደበኛ የትምህርት መርሃግብር አካል ሆነው እንደሚሰጡ ተነግሯል። መረጃው የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ነው
oroORO
Scroll to Top