Mols.gov.et

ከውጭ ሀገር የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ተወካዮች ጋር …

August 26, 2025
ከውጭ ሀገር የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ባለቤቶች እና ተወካዮች ጋር በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች በአዲሱ አዋጅ አተገባበር አንኳር ጉዳዬች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ ዜጎች ተንቀሳቅሶ የመስራት ህገመንገስታዊ መብት አላቸው፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ጠንካራ የህግ መሰረት እንዲኖረው ተደርጓል፡፡ በቅርቡ የፀደቀው የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ከኤጀንሲዎች አኳያ ፍትሃዊ ተሳትፎንና ተጠቃሚነትን ያበረታታል፡፡ የመጨረሻ ግቡም የዜጎችን ክብር፣ መብት፣ ደህንትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማሳደግ ነው፡፡ የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎቻችንም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ይፈጥራል፡፡ ለአፈፃፀሙ ውጤታማነት መንግስት እና ኤጀንሲዎች ብቻ ሳይሆኑ የስምሪቱ ተጠቃሚ ዜጎችም ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ስለሆነም ዜጎች ለየትኛውም የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ አማራጭን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
oroORO
Scroll to Top