Mols.gov.et

ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለም የሥራ ገበያን ለመጠቀም ዜጎችን በክህሎት የማብቃት…

September 20, 2024
ከሀገር ውስጥ ባለፈ የዓለም የሥራ ገበያን ለመጠቀም ዜጎችን በክህሎት የማብቃት… የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሥራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በውጭ ሀገራት ከሚፈጠሩ የሥራ ዕድሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል አንዱ ነው፡፡ ዜጎች ክብራቸውና ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ውጭ ሀገራት እንዲጓዙ ከማድረግ ጀምሮ በመዳረሻ ሀገራት የሚኖራቸው ቆይታም ደህንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት በሚኒስቴር መ/ቤቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ሚኒስቴር መ/ቤቱ የውል ስምምነት ወደፈፀመባቸው ሀገራት የሚጓዙ ዜጎች በሚሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ብቁ ለመሆን የሚያስችላቸው የክህሎት ሥልጠና በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ የክህሎት ስልጠናውን እየሰጡ ከሚገኙ ተቋማት መካከል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋም የሆነው የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢኒስቲትዩት አንዱ ነው፡፡ ኢኒስቲትዩቱ ከሃምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሦስት ዙር ከአንድ ሺ ለሚነልጡ ሰልጣኞች የአረብኛ ቋንቋን ጫምሮ በቤት አያያዝ፣ በህፃናትና አዛውንት እንክብካቤና በምግብ ዝግጅት የክህሎት ሥልጠናን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሂደቱን ፈጣንና ቀልጣፈ ለማድረግ እንዲቻልም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጠና ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል ጋር በመተባበር ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የብቃት ምዘና በኢኒስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ በቀጣይ ለ 400 ሰልጣኞች በአራተኛ ዙር ሥልጠናውን ለማስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ከኢኒስቲትዩቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
oroORO
Scroll to Top