Mols.gov.et

በጀት ዓመቱ ሚኒስቴሩ የጀመራቸው ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ውጤት ተቀይረው ማየት የጀመርንበት ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሥራና ክህሎት ሚኒስትር

September 3, 2024
በጀት ዓመቱ ሚኒስቴሩ የጀመራቸው ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ውጤት ተቀይረው ማየት የጀመርንበት ነው። ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የሚኒስቴሩ አመራሮች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች፣ የክልል እና ከተማ አስተዳደር ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል አፈጻጸሙን አስመልክተው ባቀረቡት ገለጻ፤ ሚኒስቴሩ በ2016 በጀት ዓመት በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተጀመሩ ትላልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ሥራዎች ወደ ተግባር ተሸጋግረው ውጤት ማስመዝገብ መጀመራቸውን ገልጸዋል። በክህሎት ልማት ዘርፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተኪ ምርት በማምረት የኩባንያ መፈልፈያ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች፣ ኢንተርኘሪነሪያል የሆኑ ተቋማት ለመገንባት የተሄደበት ርቀት፣ ተቋማቱ አካባቢያዊ ጸጋ መሠረት አድርገው እንዲለሙ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች እንዲሁም ውጤታማ አጫጭር እና መደበኛ ስልጠናዎች ላይ የሚቆጠር ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል። ከሥራና ሥራ ሥምሪት አኳያ ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ያረጋገጠ ጥራት ያለው የሥራ ሥምሪት በሀገር ውስጥም በውጭ ሀገር የተመዘገበበት በጀት ዓመት ነበር ብለዋል። በተለይ በጀት ዓመቱ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት በተጨማሪ መዳረሻ ሀገራት በማስፋት የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ዜጎች በተዘረጋው የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመላክ ስምምነቶች የተደረጉበት ወደ ሥራም የተገባበት መሆኑንም ተናግረዋል። በአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍም የኢንዱስትሪ ሰላም ለማረጋገጥ እና ምርታማነትን መሠረት ያደረጉ ጅምር ጥረቶች የተደረጉበት፣ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤንነት እንዲሁም የመደራጀት ምጣኔ የመሣሰሉ ተግባራት ላይ አበረታች ስኬት መመዝገቡንም አብራርተዋል። በበጀት ዓመቱ በየዘርፋ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ በዚህ መድረክ ለውይይት ቀርበው የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ በቀጣይ የእቅድ አካል አድርጎ ለመፍታት ይሰራል ብለዋል።
oroORO
Scroll to Top