Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡

January 17, 2025
ያለንን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ማላቅ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ ጋር ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት በውይይታቸው ላይ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ እያከናወናቸው ያሉ የሪፎርም ሥራዎችንና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫችንን ከማየት ባለፈም ረዥም ጊዜ ባስቆጠረው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችንም ተመልክተናል ብለዋል ፡፡ በቀጣይም የኢንተርፕሪነርሺፕ ስነ-ምህዳሩን ምቹ በማድረግ በተለይ የሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ማሳደግ በሚያስችሉ የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ጨምሮ በቀጣይ በሚለዩ የትብብር መስኮች ላይ በጋር ለመሥራት ተግባብተናል፡፡ በኢትዮጵያ የሲውዲን አምባሳደር ሃንስ ሄንሪክ የተጀመሩ ሥራዎችን በማጠናከርና በማስፋት የሁለትዮሽ ስትራቴጂያዊ አጋርነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ላሳዩት ቁርጠኝነትም አመስግነዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top