Mols.gov.et

በሥራ አውደ ርዕዩ ከ20 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ

November 17, 2025
በሥራ አውደ ርዕዩ ከ20 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል በመፍጠር በስኬት መጠናቀቁ ተገለፀ በከተማዋ ሰሞኑን ሲካሄድ የቆየው የሥራ አውደ ርዕይ በስኬት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው በከተማዋ በሚገኙ አስራ አንዱም ክፍላተ ከተሞች ቀጣሪ ድርጅቶችን ከስራ ፈላጊ ዜጎች ጋር በማገናኘት እንደየ ክህሎታቸውና እንደ ቀጣሪ ድርጅቶች የሰው ኃይል ፍላጎት የተካሄደው አውደ ርዕይ ተጠናቋል። አውደ ርዕዩ ስራ ፈላጊ እና ቀጣሪ ድርጅቶችን በአንድ ቦታ በማገናኘት የከተማዋን ሥራ አጥ ዜጋ ወደ ሥራ በማሰማራት ሂደት ትልቅ ድርሻ አለው። በከተማዋ 17ሺ600 ዜጎችን በስራ አውደ ርዕዩ ለማሳተፍ ታቅዶ ከዕቅድ በላይ በመፈፀም 20ሺ522 ወይም የዕቅዱን 117 በመቶ መፈፀም መቻሉ ተጠቁሟል። በተመሳሳይ በአውደ ርዕዩ ከ100 እስከ 200 ቀጣሪ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ዝቅተኛው የደመወዝ መጠን 4ሺ እንዲሁም ከፍተኛው የደመወዝ መጠን ደግሞ 10ሺ እና ከዚያ በላይ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል። የሥራ አውደ ርዕዩ መጠናቀቁን ተከትሎ በአንድ ጀንበር ለ20ሺ900 ዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
oroORO
Scroll to Top