ሙያ በፈጠራ ሲታገዘ ወጣቶች ኑሯቸውን በቀላሉ የሚለውጡበት ትልቅ ዘርፍ ነው፡፡ ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ
April 24, 2025

ሙያ በፈጠራ ሲታገዘ ወጣቶች ኑሯቸውን በቀላሉ የሚለውጡበት ትልቅ ዘርፍ ነው፡፡
ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ
የሶማሊ ክልል የክህሎትና የስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ያዘጋጀው 4ኛ ዙር ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች እና የአካባቢ ምርምር ስራዎች ውድድና ኤግዚቢሽን መድረክ በጅግጅጋ ተጀምሯል፡፡
በመድረኩ ላይ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድን ጨምሮ የተለያዩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የሥራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በመድረኩ የተገኙት
የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዓለም ላይ ትልቁ የሞያ መስክ የእጅ ሙያ ነው፡፡ የእጅ ሙያ ክህሎት ዳብሮ በፈጠራ ውጤት ሲታገዘ ወጣቶች ኑሯቸውን በቀላሉ የሚለውጡበት ትልቅ ዘርፍ ነው ብለዋል ።
በሶማሊ ክልል በሚገኙ 17 የቴክኒክና ሞያ ኮሌጆችን አቅም ማሳደግ ይገባል፡፡ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ምርምሮችን ማበረታታት፣ ማነቃቃት፣ የማሳደግና የመደገፍ ስራ በቀጣዩ የበጀት ዓመትም በትኩረት እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ ክህሎትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ጌይድ በበኩላቸው፤ የውድድሩ ዓላማ በክልሉ የሚገኙ የቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የፈጠራ አቅምን ማሳደግ በማሳደግ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሐገር ውስጥ ምርት መተካት ነው ብለዋል ።
በመርሐግብሩ 38 የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የቀረበ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 34 መምህራን ፣ 7 ተማሪዎች ፣ 2 ማህበራት እንዲሁም ሌሎችም የተሳተፍበት አውደ ርዕይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እንደተጎበኙ የክልሉ መገናኛ ብሁሃን ኤጀንሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

















