Mols.gov.et

ህዳሴ የዛሬው ትውልድ ታሪክን ከመዘከር የራሱን ታሪክ ወደ መጻፍ ያሸጋገረ ድንቅ የትውልድ አሻራ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

September 19, 2025
ህዳሴ የዛሬው ትውልድ ታሪክን ከመዘከር የራሱን ታሪክ ወደ መጻፍ ያሸጋገረ ድንቅ የትውልድ አሻራ ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ህዳሴ በትውልድ ቅብብሎሽ እውን የሆነ እና የዛሬው ትውልድም ታሪክን ከመዘከር የራሱን ታሪክ ወደ መጻፍ ያሸጋገረ ድንቅ የትውልድ አሻራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እንደ ሀገር የአይቻልም መንፈስ የሰበርንበት መቻላችን በተግባር ያረጋገጥንበት ነውም ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ግዙፉን ፕሮጀክት በራስ አቅም እውን ማድረግ የኢትዮጵያ ወዳጆቿ ይበልጥ እንዲወዷት በሌላ አይን የሚመለከቷት ደግሞ ደግመው ደጋግመው ቆም ብለው እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ይህንን መልከ ብዙ ትርጉም ያለው ግድብ ማጠናቀቃችን የሀገራችን የማንሰራራት ጉዞ ጉልህ ማሳያ ነው ሲሉም ገልፀዋል፡፡ አሁን ያለን እድለኛ ትውልዶች ነን ያሉት ክብርት ሚኒስትር ለሀገራችን ብልጽግና የተወጠኑ እና እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎችን በመደገፍ በሀገራችን ብልጽግና ላይ ደማቅ አሻራ ማኖር ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top