የኢስዋቲኒው ጠቅላይ ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሪፎርም ሥራዎችን አደነቁ
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ራስል ድላሚኒን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። በዚህም የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎችን እንዲሁም የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የኢስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ድላሚኒ እና ልዑካቸው የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩትንም ጎብኝተዋል።
በዚህም ራስል ድላሚኒ ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ የጀመረችው የለውጥ ጉዞ እጅግ አመርቂ እንደሆነ ገልጸው በቀጣይ በዘርፉ የትብብር ማዕቀፎችን በመቅረጽ በቅንጅት ለመሥራት ዝግጅ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህ ትብብርም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክርና የጋራ ተጠቃሚነትን እንደሚያሰፋ ተስፋም አመላክተዋል።