Mols.gov.et

ትውልድን ከሙያና ንግድ ጋር ያሰናሰለው ተሞክሮ !

June 23 , 2023 

ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለንን አጋርነት እና ትብብር ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመው የሥራ ጉብኝት ዛሬም ቀጥሎ በትሪስቲን ባቫሪያ የሚገኘውን ትረስትን የቴክኒክ ማሰልጠኛ ተቋም እና ስምንት ትውልድን ከሙያና ንግድ ጋር አሰናስሎ ዛሬ ላይ የደረሰ ውጤታማ የቤተሰብ የእንጨት ውጤቶች ንግድ ስራ ተመልክተናል፡፡ የንግድ ድርጅቱ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በእንጨት ሥራ ለሚሰለጥኑ የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ሁነኛ የተግባር ሥልጠና ቦታ ሆኖም አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህም ትውልዱን በሙያ የበቃ እንዲሆን ከማድረግ አኳያ በየደረጃው በሚገኙ መሰል ተቋማት ውስጥ እንደ ባህል ሆኖ የሚተገበር ነው፡፡፡ እንደ ዘርፍ ከጀመርናቸው የሪፎርም አጀንዳዎቻችን መካከል ሙያና ሙያተኛ ላይ ያለውን አሉታዊ አመለካከት በመስበር ከራስ አልፎ ለሀገር የሚተርፍ እጀ ወርቅ ባለሙያዎችን ማፍራት፣ የሥራ ባህላችን ላይ መሰረታዊ ለውጥ የሚፈጥሩ ተግባራትን መከወን እንዲሁም የቤተሰብ ንግድን በሰፊው ማስተዋወቅ ይገኙበታል፡፡ በየደረጃው ያሉ ተቋሞቻችና ኢንዱስትሪዎቻችን ከዛሬ ተሻግሮ ለትውልድ በሚተርፈው ትርፋማነታቸው ላይ እንዲያተኩሩ ብዙ መስራት እንዳለብን እና የጀማመርናቸው የሪፎርም ሥራዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ የትሪስቲን ባቫሪያ ጉብኝታችን አመላክቶናል፡፡
oroORO
Scroll to Top