Mols.gov.et

በክልሉ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። ክቡር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር

July 27, 2025
በክልሉ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሥራ ዕድል ተፈጥሯል። ክቡር አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በአማራ ክልል 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አረጋ ከበደ ገለፁ። የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ አረጋ ከበደ፤ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት በእልህና በቁጭት ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል ብለዋል። የፀጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች ማኅበረሰቡ ሰላምና ልማት ወዳድነቱን በግልፅ አሳይቷል ነው ያሉት። ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የዋጋ ንረትን ለመቀነስ፣ ለዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር፣ የገቢ እና የወጪ ንግድ ሚዛንን ለማስጠበቅ እንዲሁም የመንግስት ወጪ እና ገቢን ለማመጣጠን በትኩረት መሰራቱን ገልጸዋል። የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለማቃለል በየዘርፉ ከተሠሩ ሥራዎች በተጨማሪ 1 ቢሊየን ብር ያህል የመንግሥት ተዘዋዋሪ በጀት ተመድቦ መሠራቱን አንስተዋል። የሥራ አጥነት ችግርን ለመቀነስ ነባራዊ ሁኔታውን ከግምት ውስጥ ያስገባ እቅድ ተዘጋጅቶ በመሰራቱ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ 817 ሺህ 41 የሚሆነው ቋሚ የሥራ እድል መሆኑን ጠቁመዋል። ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥም 64 ሺህ 820 የሚሆነው በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እንደሆነ የፋና ዘገባ ያመላክታል። ሀምሌ 20/2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
oroORO
Scroll to Top