Mols.gov.et

በኬንያ የባርቤዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ ተወካይ…

March 21, 2025
በኬንያ የባርቤዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ ተወካይ ክቡር ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ ጋር በትብብር መሥራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ በቅርቡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድና የባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብርት ሚያ አሞር ሞተሌ የነበራቸውን የሁለትዬሽ ግንኙነት ተከትሎ በሰው ሀብት ልማትና ስምሪት ረገድ ከክብርት ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሌ ጋር መወያየታችን ይታወሳል:: የዛሬው ውይይት የሰው ሀይል ልማትና ስምሪት ዝርዝር አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ሲሆን ወደ ተግባር የሚሸጋገርበትን ውጤታማ ምክክር አድርገናል፡፡ በኬንያ የባርቤዶስ ከፍተኛ ኮሚሽነር እና በናይሮቢ የተባበሩት መንግስታት ቋሚ ተወካይ ክቡር ዊሊያም አሌክሳንደር ማክዶናልድ በትብብር ለመሥራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡ የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
oroORO
Scroll to Top