Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት የልማት ትብብር ሃላፊ…

February 26, 2024
በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት የልማት ትብብር ሃላፊ ስቴፋን ሎክ (ዶ/ር) ጋር በሠራተኛ ፍልሰት አስተዳደር ላይ አተኩሮ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚኒስትሮች ፎረም አበርክቶን ለማሳደግ የሚያስችል ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ በውይይታችን መደበኛና ህጋዊ ፍልሰትን ማስተዳደር የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት የቀጠናው ብቻ ሳይሆን የዓለም ጉዳይ በመሆኑ የሰለጠና እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት የተጀመሩ ስራዎችን በትብብር መስራት እንደሚገባ ተመልክተናል፡፡ በዚህም ህብረቱ ከምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሠራተኞች ፍልሰት የሚኒስትሮች ፎረም ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተግባብተናል፡፡ የአውሮፓ ህብረት የልማት ትብብር ሃላፊ ስቴፋን ሎክ (ዶ/ር) በፍልሰት አስተዳደር ዙሪያ የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሚኒስትሮች ፎረም ጋር በትብብር ለመስራት ላሳዩን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ!
oroORO
Scroll to Top