Mols.gov.et

በአሠሪዎች እና ሠራተኞች መካከል ያለው ትብብር…

December 4, 2023
“በአሠሪዎች እና ሠራተኞች መካከል ያለው ትብብር የሃገሪቱን የሥራ ምህዳር ብሎም ሀገራዊ ምርታማነትን በመወሰን ረገድ ዕጅግ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ” ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ኢትዮጵያ የዓለም ሥራ ድርጅት አባል የሆነችበት መቶኛ ዓመት ክብረ በዓል እና ብሄራዊ የአሠሪና ሠራተኛ ጉባኤ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የዓለም ሥራ ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን፣ የኢትጵያ አሠሪ ፌዴሬሽን ኮንፌዴሬሽን፣ የኢትዮጵያ አሰሪዎች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በጋራ ባዘጋጁት በዚህ መድረክ በዓለም ሥራ ድርጅት የአፍረካ ዳይሬክተር ፋንፋን ርዩንዶ ካዩራጓ ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ድርጅቶች የሥራ ኋላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የእንኳን አደረሰን መልዕክት እና የመክፈቻ ንግግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት ፣ በአሠሪዎች እና ሠራተኞች መካከል ያለው ትብብር የሃገሪቱን የሥራ ምህዳር ብሎም ሀገራዊ ምርታማነትን በመወሰን ረገድ ዕጅግ ወሳኝ በመሆኑ ክብረ በዓሉ እና ጉባኤው ኢትዮጵያ በማህበራዊ ምክክር፣ ዘላቂ የኢንዱስትሪ ሰላምን በማረጋገጥና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ያላትን ቁርጠኛነት የምታሳይበት ነው፡፡ ከዓለም ሥራ ድርጅት የነበረን ዕድሜ ጠገብ አጋርነትና ትብብር ይበልጥ የምናጸናበት እና አባቶቻችን በማህበራዊ ውይይቶች እና በሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ለ100 ዓመታት ያሸጋገሩልን ታሪክ እኛም ይበልጥ በማጠናከር ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያ የምናስተላልፍበት የማዕዘን ድንጋይ ይሆናል ብለዋል፡፡
oroORO
Scroll to Top