Mols.gov.et

የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር…

January 26, 2024
የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር አገልግሎት ተደራሽነቱን ለማስፋት በዘርፉ ብቁና በቂ የሰለጠነ የሰው ሃይል በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለማፍራት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በመድረኩ በአምስት ክልሎች ከሚገኙ 12 የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተወጣጡ 48 ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሰሪና ሠራተኛ ዘርፍ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ሥራ አሰፈጻሚ ተካልኝ አያሌው (ዶ/ር) በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እሰራ ነው፡፡ አሁን የተሰጠው ስልጠና ዓላማ በሀገሪቱ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት እና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ፣ ለአዲስ ተመራቂ ወጣት ባለሙያዎች በሙያ ደህንነትና ጤንነት የትምህርት መስክ የሥራ እድል ለመፍጠርና በዚህም በኢንዱስትሪዎች የሥራ ቦታዎችን ምቹ፣ ከሙያ ጠንቆችና ከሥራ ላይ አደጋዎች የተጠበቁ እንዲሆኑና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር የበኩሉን ለመወጣት ያስችላል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top