Mols.gov.et

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች

May 21, 2026
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች «የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት» አገራዊ ኤግዚቢሽን ጎበኙ ኤግዚቢሽኑ በኢትዮጵያ አስተማማኝ፣ ዘመናዊና የተቀናጀ የስታቲስቲክስ መረጃ ሥርዓት ለመገንባት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በመረጃና በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ ፖሊሲዎችንና የልማት ዕቅዶችን ለመቅረጽ የተከናወኑ ስኬታማ ሥራዎች ለዕይታ በቅተውበታል። በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለጸው፤ መረጃ አገራዊ ራዕይ የሆነውን ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የመገንባትና የፖሊሲ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞ ዋነኛ ግብዓት ነው። የዜጎችን እውቀትና ክህሎት በተደራጀ መንገድ በመጠቀም መረጃዎችን በሳይንሳዊ መንገድ የመሰብሰብ፣ የመተንተን እና በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን የማውጣት ልምድን ለማሳደግ የሚያስችል ሰፊ መሠረት እየተጣለ እንደሚገኝ ተመላክቷል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ይህንን አገራዊ ራዕይ ለማሳካትና በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና በኢንዱስትሪ ሰላም ዙሪያ የሚወጡ ፖሊሲዎችና ዕቅዶች ትክክለኛ መረጃን መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑ በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
en_USEN
Scroll to Top