Mols.gov.et

የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ በየፈርጁ …

August 25, 2025
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ በየፈርጁ … በቻይና በተካሄደ የብሪክስ አባል ሀገራት የክህሎት ውድድር የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ በድል ከፍ ያደረጉ ልጆቻችንን ተቀብለን አበረታተናል። ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እያንሰራራች ነው፡፡ በብሪክስ አባል ሀገራት የክህሎት ውድድር መድረክ ላይ የተመዘገበው ውጤትም የዘርፋችንን ማንሰራራት የሚያበስር የድል ችቦ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ዓመታት ብቻ መክሊቱ እና ፍላጎቱ ያላቸውን ወጣቶች በማሰባሰብ በተሰራው ሥራ ከምስለ-ምርት ያለፉና ወደ ብዝሃ ምርትነት የተቀየሩ ቴክኖሎጂዎችን መስራት ተችሏል፡፡ ብዙዎቹ የውጪ ምርትን የሚተኩ፣ ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን የሚያቀላጥፉ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች ናቸው፡፡ በብሪክስ አባል ሀገራት የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ያደረጉት ወጣቶችም ” *_የክህሎት ኢትዮጵያ_* ” መርሀ ግብር ውጤቶች ናቸው፡፡ ወጣት ዘላለም እንዳለው፣ ወጣት አቤኔዘር ተከስተ እና ወጣት ነቢሀ ነስሩ ለሀገራችን ወርቅ፣ ብር እና ነሃስ በማምጣት ለብዙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ፈር ቀዳጅ የሆነ ውጤት በማምጣታችሁ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!
en_USEN
Scroll to Top